Home Integration Strategy

Strategy

E-mail Print PDF
ኢትዮጵያ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለመሰለፍ የተቀናጀ የመሠረተ ልማት ቀድሞ
መገኘት ለሌሎች የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎቿ ዕድገት ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ይታመናል፡፡
በዚህም መሠረት በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድ ዘመን
ትኩረት ከተሰጣቸው አብይ ዘርፎች ውስጥ አንዱ የኢኮኖሚ መሰረተ ልማቶች ግንባታ ዘርፍ
ነው፡፡ ዘርፉ የኢኮኖሚውን ዕድገት በማስቀጠል እና ይበልጥ ተተኪ የሌለው የደጋፊነት ሚናውን
በላቀ ሁኔታ እንዲወጣ የሚያስችሉ የተለያዩ ውጥኖችን በመያዝ ለተግባራዊነታቸው ርብርቦሽ
እየተደረገ ይገኛል፡፡
የኢኮኖሚ መሠረተ ልማት በ2017 ሀገራችንን ዝቅተኛ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ
ለማሰለፍ የተቀመጠውን ራዕይ ለማሳካት የሚያስፈልገውን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣት
በሚደግፍ ደረጃ በጥራትና በፍጥነት እንዲያድግና ኢኮኖሚው ተወዳዳሪ እንዲሆን እንዲሁም ሁሉን
አቀፍ ዕድገት እንዲመጣ ለማድረግ የላቀ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል፡፡ የመሠረተ
ልማቶች ዕድገት ኢንቨስትመንትን ለመሳብ፣ አዳዲስ የገበያ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ የሸቀጦች ዋጋን
ለመቀነስ፣ የተወዳዳሪነት መንፈስን ዕውን ለማድረግ፣ የቀጠና የኢኮኖሚ ትስስርን ለመፍጠር ካለው
ፋይዳ አኳያ
 የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ፣
 የባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ፣
 የውሃ አቅርቦት መሰረተ ልማት ግንባታ
 የአየር ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ግንባታ፣
 የኃይል ማመንጫ እና አገልግሎት መሰረተ ልማት ግንባታ እና
 የቴሌኮሙኒኬሽን መሠረተ ልማት ግንባታ ሥራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲስፋፋ
የሚሰራ ነው፡፡
ጠንካራ የማስፈጸም አቅም ያለው ተቋም በመፍጠር፣ የህዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን
በማረጋገጥ፣ የተቀናጀ የመሠረተ ልማት ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ ነው፡፡
በዚሁ መሰረት በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የመሠረተ ልማቶች
ማስፋፋት ሥራ በሰፊው እየተከናወነ ነው፡፡ በመንገድ ግንባታ ዘርፍ ጠቅላላ የመንገድ ርዝመቱ
1
በ2007 ከነበረበት የ110,000 ኪ.ሜ በ2012 ወደ 220,000 ኪ.ሜ ለማሳደግ፤ በምድር ባቡር
ግንባታ ዘርፍ በአምስት ኮሪደሮችና ስድስት መስመሮች በጠቅላላው የ2,741 ኪ.ሜ ሃገራዊ የባቡር
ኔትወርክ ግንባታ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው፡፡

የአየር ትራንስፖርትን በተመለከተ በ2007 የነበሩትን 20 ኤርፖርቶች በ2012 ወደ 25 ከፍ
ማድረግ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎትና ኃይል ማመንጨትን በተመለከተ የኤሌክትሪክ ኃይል
የማመንጨት አቅምን በ2007 ከነበረበት 4,180 ሜጋ ዋት በ2012 ወደ 17,208 ሜጋ ዋት
ማድረስ፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሽፋንን በ2007 ከነበረበት 60 በመቶ በ2012 ወደ 90 በመቶ፣
የሀይል ማሰራጫ መስመር ዝርጋታ ከነበረበት 1,608 ኪ.ሜ ወደ 21,728 ኪ.ሜ ከፍ ለማድረግ፤
በቴሌ ኮሙኒኬሽን ንዑስ ዘርፍ የሞባይል ስልክ፣ የብሮድባንድ ኢንተርኔትና ዳታ እና የመደበኛ
ስልክ ደንበኞችን ብዛት በቅደም ተከተል በ2007 ከነበረበት 38.8 ሚሊዮን፣1.91 ሚሊዮን እና
0.838 ሚሊዮን ደንበኞች በ2012 ወደ 103፣ 39.1 እና 10.4 ሚሊዮን ከፍ ለማድረግ ታቅዷል፡፡
እነዚህ ግዙፍ የመሰረተ ልማት ስራዎች ሲከናወኑ አንዱ በሌላው ላይ ጉዳት ምክንያት
የአገልግሎቶች መቆራረጥና የአካባቢ ብክለት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ እንዲሁም
በመሠረተ ልማት ግንባታ ወቅት በሚነሱ የመሬት ይዞታዎች እና የንብረት ካሳ አገማመት
በሀገሪቱ ከፍተኛ ልዩነት እና የአፈፃፀም መጓተት መኖር በተጠቃሚውና በመንግስት ላይ ከጊዜ ወደ
ጊዜ ውስብስብ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር እያስከተለ መምጣቱን ህብረተሰቡም ሆነ መንግስት
በየጊዜው እየገለፀ ነው፡፡ እነዚህን ተግዳሮቶችን ሌሎች ችግሮችን የሚፈታ እንዲሁም የመሰረተ
ልማት ስራዎች ወደፊት ከዚህ በጨመረ መጠን እየተሰሩ ስለሚቀጥሉ በተቀናጀና ውስን ሀብትን
ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም እንዲያስችል የመሠረተ ልማት ስራዎችን የሚያስተባብር
የፌደራል የተቀናጀ መሠረተ ልማቶች ማስተባበሪያ ኤጀንሲ ተቋቁሞ ሥራ ጀምሯል፤ ይህ የሶስት
ዓመት (2010-2012) ስትራቴጂክ ዕቅድ እነዚህን ስራዎች በታቀደ መልኩ ለማከናወን እንዲረዳ
የተዘጋጀ ነው፡፡

ኢትዮጵያ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለመሰለፍ የተቀናጀ የመሠረተ ልማት ቀድሞ መገኘት ለሌሎች የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎቿ ዕድገት ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ይታመናል፡፡ በዚህም መሠረት በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድ ዘመን ትኩረት ከተሰጣቸው አብይ ዘርፎች ውስጥ አንዱ የኢኮኖሚ መሰረተ ልማቶች ግንባታ ዘርፍ ነው፡፡ ዘርፉ የኢኮኖሚውን ዕድገት በማስቀጠል እና ይበልጥ ተተኪ የሌለው የደጋፊነት ሚናውን በላቀ ሁኔታ እንዲወጣ የሚያስችሉ የተለያዩ ውጥኖችን በመያዝ ለተግባራዊነታቸው ርብርቦሽ እየተደረገ ይገኛል፡፡

የኢኮኖሚ መሠረተ ልማት በ2017 ሀገራችንን ዝቅተኛ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለማሰለፍ የተቀመጠውን ራዕይ ለማሳካት የሚያስፈልገውን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣት በሚደግፍ ደረጃ በጥራትና በፍጥነት እንዲያድግና ኢኮኖሚው ተወዳዳሪ እንዲሆን እንዲሁም ሁሉን አቀፍ ዕድገት እንዲመጣ ለማድረግ የላቀ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል፡፡ የመሠረተ ልማቶች ዕድገት ኢንቨስትመንትን ለመሳብ፣ አዳዲስ የገበያ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ የሸቀጦች ዋጋን ለመቀነስ፣ የተወዳዳሪነት መንፈስን ዕውን ለማድረግ፣ የቀጠና የኢኮኖሚ ትስስርን ለመፍጠር ካለው ፋይዳ አኳያ

  • የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ፣
  • የባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ፣
  • የውሃ አቅርቦት መሰረተ ልማት ግንባታ
  • የአየር ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ግንባታ፣
  • የኃይል ማመንጫ እና አገልግሎት መሰረተ ልማት ግንባታ እና
  • የቴሌኮሙኒኬሽን መሠረተ ልማት ግንባታ ሥራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲስፋፋ የሚሰራ ነው፡፡

ጠንካራ የማስፈጸም አቅም ያለው ተቋም በመፍጠር፣ የህዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ፣ የተቀናጀ የመሠረተ ልማት ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የመሠረተ ልማቶች

ማስፋፋት ሥራ በሰፊው እየተከናወነ ነው፡፡ በመንገድ ግንባታ ዘርፍ ጠቅላላ የመንገድ ርዝመቱ በ2007 ከነበረበት የ110,000 ኪ.ሜ በ2012 ወደ 220,000 ኪ.ሜ ለማሳደግ፤ በምድር ባቡር ግንባታ ዘርፍ በአምስት ኮሪደሮችና ስድስት መስመሮች በጠቅላላው የ2,741 ኪ.ሜ ሃገራዊ የባቡር ኔትወርክ ግንባታ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው፡፡

የአየር ትራንስፖርትን በተመለከተ በ2007 የነበሩትን 20 ኤርፖርቶች በ2012 ወደ 25 ከፍ ማድረግ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎትና ኃይል ማመንጨትን በተመለከተ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅምን በ2007 ከነበረበት 4,180 ሜጋ ዋት በ2012 ወደ 17,208 ሜጋ ዋት ማድረስ፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሽፋንን በ2007 ከነበረበት 60 በመቶ በ2012 ወደ 90 በመቶ፣

የሀይል ማሰራጫ መስመር ዝርጋታ ከነበረበት 1,608 ኪ.ሜ ወደ 21,728 ኪ.ሜ ከፍ ለማድረግ፤ በቴሌ ኮሙኒኬሽን ንዑስ ዘርፍ የሞባይል ስልክ፣ የብሮድባንድ ኢንተርኔትና ዳታ እና የመደበኛ ስልክ ደንበኞችን ብዛት በቅደም ተከተል በ2007 ከነበረበት 38.8 ሚሊዮን፣1.91 ሚሊዮን እና 0.838 ሚሊዮን ደንበኞች በ2012 ወደ 103፣ 39.1 እና 10.4 ሚሊዮን ከፍ ለማድረግ ታቅዷል፡፡

እነዚህ ግዙፍ የመሰረተ ልማት ስራዎች ሲከናወኑ አንዱ በሌላው ላይ ጉዳት ምክንያት የአገልግሎቶች መቆራረጥና የአካባቢ ብክለት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ እንዲሁም በመሠረተ ልማት ግንባታ ወቅት በሚነሱ የመሬት ይዞታዎች እና የንብረት ካሳ አገማመት በሀገሪቱ ከፍተኛ ልዩነት እና የአፈፃፀም መጓተት መኖር በተጠቃሚውና በመንግስት ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ውስብስብ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር እያስከተለ መምጣቱን ህብረተሰቡም ሆነ መንግስት በየጊዜው እየገለፀ ነው፡፡ እነዚህን ተግዳሮቶችን ሌሎች ችግሮችን የሚፈታ እንዲሁም የመሰረተ ልማት ስራዎች ወደፊት ከዚህ በጨመረ መጠን እየተሰሩ ስለሚቀጥሉ በተቀናጀና ውስን ሀብትን ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም እንዲያስችል የመሠረተ ልማት ስራዎችን የሚያስተባብር የፌደራል የተቀናጀ መሠረተ ልማቶች ማስተባበሪያ ኤጀንሲ ተቋቁሞ ሥራ ጀምሯል:: ይህ የሶስት ዓመት (2010-2012) ስትራቴጂክ ዕቅድ እነዚህን ስራዎች በታቀደ መልኩ ለማከናወን እንዲረዳ የተዘጋጀ ነው፡፡

Last Updated ( Thursday, 13 July 2017 12:57 )  

Focus

integration

master_plan

compensation

Subscribe


Name:
Email:


    Home | Site Map | Links | Contact us
Copyright © 2017 Federal Integrated Infrastructure Development Coordinating Agency (FIIDCA)